በመላው የዋሽንግተን ግዛት የ Help Me Grow ፕሮግራምን ለማስተባበር ከምናደርገው ጥረት አንዱ ክፍል፡ ስድስት የዋሽንግተንን Help Me Grow ዋሽንግተን የድርጊት ቡድኖችቡድን ፈጥረናል። በ የድርጊት ቡድን መሪየሚመራ እያንዳንዱ የድርጊት ቡድን የየእራሳቸውን የ Help Me Grow ሞዴል ንድፍ እና እድገትን በተመለከተ ምክር ይሰጣሉ። በተጨማሪም ሁሉም ቡድኖች እንደ አንድ ትልቅ ቡድን በመሆን ዝማኔዎችን ለማቅረብ፣ ሃሳቦችን ለመለዋወጥ እና ግንኙነት ለመፍጠር አዘውትረው ይሰበሰባሉ።

የድርጊት ቡድንን ለመቀላቀል ፍላጎት ካሎት፡ እባክዎ፡-

  1. ከዚህ በታች ያለውን የተግባር ቡድን መግለጫ ያንብቡ እና የቅጥር በራሪ ወረቀቱን ( በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ).
  2. ይመልከቱ የዋሽንግተን Help Me Grow ስርዓትን መገንባት የሚለው ዌቢናር (ወይ PowerPoint ን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓኒሽ).
  3. በኦላይን ላይ የፍላጎት ቅጹን ይሙሉ (በሁለቱም በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋ)።

የተግባር ቡድኖች የዘር እኩልነት እና የመደመር እሴቶች ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ፡ ዓላማውም ሁሉንም ከቅድመ ወሊድ እስከ 5 የሚደርሱ ህጻናትን የሚያገለግል ጸረ-ዘረኝነት ስርዓት ለመፍጠር፣ ብዙ እድል በሌላቸው ልጆች ላይ ያተኮሩ ናቸው። ለተግባር ቡድን አባላት የጉዞ እና የልጆች እንክብካቤ ድጎማዎች፣ የትርጉም አገልግሎቶች እና የቴክኖሎጂ እርዳታ ይሰጣል።

ስለ Help Me Grow Action Team Leads የበለጠ ይወቁ

የእኛ የዘር ግንኙነት ቡድኖች (Racial Affinity Groups) በተመለከተ የበለጠ ይረዱ


የዋሽንግተን የ Help Me Grow የተግባር ቡድኖች፦

የሕጻናት ጤና አጠባበቅ አቅራቢዎች ማሰራጫ

የልጅ እና የቤተሰብ ጤና አቅራቢዎችን ከ Help Me Grow ጋር ለማገናኘት ስልቶችን አዳብሩ። ይህ የመልእክት መላላኪያ ቁሳቁሶችን ማዳበርን፣ የማዳረስ ዘመቻዎችን፣ ስልጠናዎችን፣ ዝግጅቶችን እና ሌሎች ግብአቶችን ያካትታል።

ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ማዳረስ

ቤተሰቦች እና ድርጅቶች ሊገኙ የሚችሉትን ምንጮችን አስመልክቶ ግንዛቤ እንዳላቸው እና ከነሱም ጋር መገናኘታቸውን ያረጋግጡ። ይህ የመልእክት መላላኪያ መሳርያዎችን ማዳበር፣ የማዳረስ ዘመቻዎች፣ ስልጠናዎች፣ ዝግጅቶን እና ሌሎች ስለ ልጅ እድገት ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት የሚጠቅሙ ዘዴዎችን ያካትታል።

የተቀናጀ የመዳረሻ ነጥብ

ቤተሰቦች ለትናንሽ ልጆች ድጋፎችን ማግኘት እንዲችሉ፡ የተቀናጀ የመዳረሻ ስርዓትን በመላው ስቴት የሚያረጋግጡ ስልቶችን ያዘጋጃሉ። ይህ ከስቴት እና ከአካባቢው የመረጃ ማውጫዎች፣ የቴክኖሎጂ መድረኮች እና የእንክብካቤ አስተባባሪዎች/የቤተሰብ የድጋፍ ምንጭ አሳሾች ጋር የተያያዙ እድሎችን እና ተግዳሮቶችን መለየትን ያካትታል። ይህ ከስቴት እና ከአካባቢው የመረጃ ማውጫዎች፣ የቴክኖሎጂ መድረኮች እና የእንክብካቤ አስተባባሪዎች/የቤተሰብ ሃብት አሳሾች ጋር የተያያዙ እድሎችን እና ተግዳሮቶችን መለየትን ያካትታል።

የውሂብ ስብስብ እና ትንተና

የ HMG ስርዓትን ያለማቋረጥ ለማሻሻል የ Help Me Grow አመልካች የመረጃ ውሂብን ይተነትናል። ይህ የስርዓት አጠቃቀም መረጃን መተንተን፣ በጊዜ ሂደት ያሉ አዝማሚያዎችን መፈለግ እና የሃብት ክፍተቶችን ለመሙላት ተጨማሪ የስርዓት ፍላጎቶችን መለየትን ይጨምራል።

እኩልነት

በ Help Me Grow ስርዓት ውስጥ እኩልነትን ለማካተት ማዕቀፎችን፣ መሳሪያዎችን፣ እና ስልቶችን ለይተው ይወቁ። HMG ዋሽንግተን ተከታታይ ስርዓቶችን፣ ድርጅታዊ እና የግለሰብ ደረጃ ስትራቴጂን እና እርምጃን እንደሚወስድ በመረዳት፡ በሁሉም ተያያዥ ዋና ክፍሎች ውስጥ የዘር እኩልነትን ለመክተት ያልማል።

ተሟጋችነት

የልጆችን፣ ቤተሰቦችን እና ማህበረሰቦችን ደህንነት የሚያሻሽሉ ሀብቶችን እና ፖሊሲዎችን ለይቶ ማወቅ እና መደገፍ። ይህ የ Help Me Grow ስርዓትን እና በ HMG በኩል ተለይተው የሚታወቁ ፍላጎቶችን መደገፍን ይጨምራል።


ስለ Help Me Grow ቡድናችን የበለጠ ይረዱ!

ከቡድኑ ጋር ይገናኙ

የ Help Me Grow የተግባር ቡድኖች በተመለከተ ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካሎት፣ እባክዎን ወደ HMGWA@withinreachwa.org.