WithinReach የዋሽንግተን ስቴት አጋር እና የ Help Me Grow አደራጅ አካል ነው። አደራጅ አካል እንደመሆኑ መጠን፡ WithinReach የክልሎቻቸውን ልዩ ፍላጎቶች እና ሀብቶች በሚያከብር መልኩ ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር በማቀድ እና በመተግበሩ የዋሽንግተን Help Me Grow ስርዓት መስፋፋትን ይመራል። እንዲሁም ድጋፍ ለሚሹ ቤተሰቦች እንደ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የመዳረሻ ነጥብ በመሆን እናገለግላለን።

የስርዓት ባለሙያ

WithinReach ከ Help Me Grow ብሄራዊ እና ከአካባቢው ማህበረሰቦች ጋር የመሳፈሪያ እና የእቅድ መሳሪያዎችን ይተገበራል፤ እንዲሁም ስራቸው በሀገር አቀፍ ደረጃ በ Help Me Grow ስርዓቶች ውስጥ ከሚገኙት ቁልፍ ባህሪያት ጋር የሚጣጣም መሆኑን ያረጋግጣል። ለአጋሮች የማሰልጠን፣ የማስተማር እና የጋራ የመማር እድሎችን እና እንዲሁም የተሰበሰቡ የድጋፍ ምንጮችን እንሰጣለን። ምርጥ ተሞክሮዎችን እንሰበስባለን እና እናካፍላለን፣ ለመረጃ መጋራት መንገዶችን እንፈጥራለን፣ እንዲሁም የመረጃ መሠረተ ልማት ድጋፍ እንሰጣለን።

ተሟጋችነት

WithinReach ከክልላዊ የቅድመ ልጅነት ተነሳሽነት ጋር የሚጣጣሙ የተግባር እና የፖሊሲ ምክሮችን ያስተዋውቃል እና ለፍትሃዊ የዋሽንግተን Help Me Grow ስርአት የጋራ ራዕይን ይገነባል። ሆን ተብሎ በእቅድ የተለያየ የቤተሰብ ድምጽ ለመስማት የሚፈልግ ፍትሃዊ ውሳኔ አሰጣጥን ለመደገፍ ከክልል እና ከስቴት ኤጀንሲዎች ጋር በመተባበር የግለሰቦችን ማህበረሰብ ፍላጎቶች የሚያንጸባርቁ እና ለሁሉም ቤተሰቦች ጠቃሚ የሆኑ ስርዓቶች መገንባት እንችላለን። ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ እንጠይቃለም እንዲሁም ሌሎች እንዲሟገቱ እናበረታታለን።

ከጤና፣ ከዕድገት፣ ከባህሪ እና ከመማር ጋር የተያያዙ የመረጃ ምንጮችን ለማወቅ ለዋሽንግተን Help Me Grow የስልክ መስመርን በስ.ቁ 1-800-322-2588 በመደወል ያግኙ። ወደዚህ የስልክ መስመር ሲደውሉ፡ ከእኛ የእንክብካቤ አስተባባሪዎች አንዱ ስጋቶችዎን ያዳምጣል እንዲሁም የቤተሰብዎን ፍላጎት ለማሟላት ተገቢውን የድጋፍ ምንጮችን እና አገልግሎቶችን ይሰጥዎታል።