የእድገት አዲስ ምዕራፍ የሚጠቁም ነጻ መተግበራያን
ይሞክሩ
የህይወት አዲስ ምእራፍ አስፈላጊ ነው! ከ CDC “ምልክቶቹን ይወቁ። አስቀድመው እርምጃ ይውሰዱ። ፕሮግራም”የሚለውን የእድገት አዲስ ምእራፍ መጠቆሚያ፡ የልጅዎን የመጀመሪያ እድገት በቀላሉ ለመከታተል እና ለማክበር ይችላሉ። ለአጠቃቀም ቀላል በሆኑ ማረጋገጫ ነጥቦችን በመጠቀም ከ 2 ወር እስከ 5 አመት ውስጥ ባለው ቁልፍ የእድገት ደረጃ ምዕራፎች የልጅዎን ምእራፎች ዝርዝሮች ይከታተሉ። እንዲሁም የልጅዎን እድገት ለማበረታታት ጠቃሚ ምክሮችን ያግኙ እንዲሁም ልጅዎ እንዴት እያደገ እንዳለ ካሳሰበዎ ምን ማድረግ እንዳለቦት ይወቁ። በዚህ መተግበሪያ ውስጥ ያሉ ፎቶግራፎች እና ቪዲዮዎች እያንዳንዱን ምዕራፍ የሚያሳዩ ሲሆን፡ የልጅዎን እድገት ለማየት እነሱን መከታተል ቀላል እና አስደሳች ነው።