ትክክለኛውን እርዳታ ማግኘት ከባድ ነው። ቀላል እንዲሆን እናደርጋለን።

የዋሽንግተን Help Me Grow ወላጆችን እና ተንከባካቢዎችን በማህበረሰባቸው ውስጥ ካሉ የድጋፍ ምንጮችን ጋር የሚያገናኝ ነጻ አገልግሎት ነው። የዋሽንግተን Help Me Grow በግዛቱ ውስጥ ከ6,000 በላይ በሆኑ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች የመረጃ ፍርግርግ የተጠናከረ ነው። Help Me Grow በስ.ቁ 1-800-322-2588 ሲደውሉ፡ የሚፈልጉትን የድጋፍ ምንጮችን እንዲያገኙ እናግዝዎታለን። የቅድሚያ የልጅነት እድገት የማጣራት ምርመራ፣ ለጤና መድህን አገልግሎት ማመልከቻ እርዳታ፣ ወይም የምግብ ባንክ ለማግኘት እገዛ፣ የወላጅነት ክፍል፣ ወይም ዝቅተኛ ዋጋ ያለው የህክምና ክሊኒክ ለማግኘት ለመርዳት ዝግጁ ነን።

ዛሬ ለመጀመር በ 1-800-322-2588 የዋሽንግተን Help Me Grow የስልክ መስመር በመደወል ደግ የሆኑ እና እውቀት ያላቸውን ሰራተኞች ያነጋግሩ!

Help Me Grow እንዴት ነው የሚሰራው?

በስቴቱ ውስጥ የት እንደሚኖሩ መሰረት በማድረግ፡ የ Help Me Grow የመረጃ ድጋፎች ለእርስዎ ይገኛሉ። ከሚፈልጓቸው ድጋፎች ጋር እርስዎን ለማገናኘት የኛ የ Help Me Grow ስልክ ቁጥር እና ሌሎች የሀገር ውስጥ ስልክ ቁጥሮችን ከዚህ በታች ተዘርዝረው ያገኛሉ።

በስቴት አቀፍ የ Help Me Grow፡ 1-800-322-2588

የ Kittitas ካውንቲ፡ 509-490-3009

የ Pierce ካውንቲ፡ 211 ይደውሉ እና Help Me Grow ይጠይቁ

Skagit ካውንቲ፡ 360-630-8352

Yakima ካውንቲ፡ 509-490-3009