ምን እንደሚጠበቅ
ከታች ያሉትን አዝራሮች ጠቅ ሲያደርጉ፡ ወደ ኦንላይን ASQ ይገባሉ። በልጅዎ ዕድሜ ላይ በመመስረት፡ እንደ "ልጅዎ በአንድ እግሩ መቆም ይችላል?" የመሳሰሉት አንዳንድ የልጅዎን የእንቅስቃሴዎች የማጠናቀቅ ችሎታ በተመለከተ ይጠየቃሉ። መልሶችዎን በመስመር ላይ ካስገቡ በኋላ፡ የእኛ የእንክብካቤ አስተባባሪዎች የ ASQ ደረጃ ይሰጣሉ እንዲሁም በአንድ ሳምንት ውስጥ ውጤቱን በተመለከተ ያነጋግርዎታል። አዳዲስ ክህሎቶችን ለመለማመድ ከልጅዎ ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታዎች እና እንቅስቃሴዎች ምክሮችን እናቀርባለን። ስለልጅዎ እድገት መማር እና መደገፍ እንዲቀጥሉ በየ 3 እና 6 ወሩ ሌላ ስክሪን እንልካለን።